በአርቲስት ታሪኩ ጋንኪሲ ስም እና ፎቶ ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንቶች!

“ድሽታ ግና” በሚል ተወዳጅ ስራው እውቅና ያገኘው አርቲስት ታሪኩ ጋንኪሲ ስሙን እና ፎቶውን በመጠቀም በርካታ የፌስቡክ አካውንቶች እንደተከፈቱ አሳውቆናል። ኢትዮጵያ ቼክ መመልከት እንደቻለው ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ሰባት አካውንቶች በስሙ ተከፍተው ይገኛሉ።

አንዳንዶቹ አካውንቶች የፖለቲካ መልእክቶች እየተላለፉባቸው ስለሚገኙ ህዝብ ይወቅልኝ ብሏል፣ ትክክለኛ የፌስቡክ አካውንቱ ይህ ብቻ እንደሆነም ገልፆልናል:

https://www.facebook.com/tariku.gankise

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::