“የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት የተለጠፈበት ድረ-ገፅ እየሰራልን አይደለም” ተማሪዎች እና ቤተሰቦች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ የሆነ ሲሆን ውጤቱ የተለጠፈበት ድረ-ገፅ ግን እየሰራ እንዳልሆነ ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል፣ በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪዎች ቤተሰቦችም ጥቆማ እያደረሱን ይገኛል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ የከተማ አስተዳደሩን የትምህርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ክፍል አናግሯል።

“የኔትወርክ ችግር አጋጥሞ ነበር፣ አሁን ግን መስራት ጀምሯል” ያሉን የክፍሉ ሀላፊ “በተጨማሪም ውጤቱ ወደየትምህርት ቤቶች ተልኳል” የሚል አጭር መልስ ሰጥተውናል።

ድረ-ገፁ ግን አሁንም እየሰራ እንዳልሆነ መመልከት ችለናል።

እንደ ቢሮው ገለፃ ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት አመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት ሆናል ብሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ 85.5% ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል ለመዛወር መቻላቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተፈና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዲናኦል ጫላ ገልጸው ነበር።

በዚህ ዙርያ ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::