የጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ በርካታ የፌስቡክ ገጾች መኖራቸውን አስተውለናል!

በጋዜጠኛዋ ስም ከተከፈቱ ገጾች መካከል ከ114 ሺህ በላይ፣ ከ88 ሺህ በላይ፣ ከ59 ሺህ በላይ እንዲሁም ከ31 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሏቸው አራት የፌስቡክ ገጾች የሚገኙ ሲሆን በየዕለቱ በርካታ መልዕክቶችን በማጋራት በሺዎች የሚቆጠር ግብረ-መልስ ያገኛሉ። ከነዚህ በተጨማሪም ከጥቂት መቶዎች እስከ አስር ሺዎች ተከታይ ያሏቸው የጋዜጠኛዋን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ በርካታ የፌስቡክ ገጾች አሉ።

ኢትዮጵያ ቼክ የፌስቡክ ገጾቹን ትክክለኛነት ለማጣራት ጋዜጠኛ ሄርሜላን ያነጋገረ ሲሆን ትክክለኛው የፌስቡክ ገጿ ከ114 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትና ከታች የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ በመከተል የሚገኘው መሆኑን አስታውቃለች (https://www.facebook.com/HermelaTV)

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራሳችንን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች እናርቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::