የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ስምና የንግድ ምልክት በመጠቀም የተከፈቱ በርከት ያሉ የቴሌግራምና የፌስቡክ አካውንቶች መኖራቸውን ተመልክተናል!

በተለይ በቴሌግራም አካውንቶቹ ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮች የሚሉና ሌሎች የማጭበርበሪያ መልዕክቶች እንደሚጋሩ አስተውለናል። የኢትዮጵያ ቼክ ተከታዮችም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ የቴሌግራምና የፌስቡክ አካውንቶችን እንድናጣራለቸው ጠይቀውናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ትክክለኛ የቴሌግራምና የፌስቡክ አካውንቶችን ለማረጋገጥ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን አነጋግሯል። የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ማናጀር ተወዳጅ እሸቱ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ትክክለኛ የቴሌግራምና የፌስቡክ እንዲሁም የትዊተር፣ የቲክቶክ፣ የሊንክድኢን፣ የኢንስታግራም አካውንቶች የሚከተሉት መሆናቸውን አስታውቀዋል።

Telegram : https://t.me/Safaricom_Ethiopia_PLC

Facebook : https://www.facebook.com/SafaricomET

Twitter : https://twitter.com/SafaricomET

TikTok: https://www.tiktok.com/@safaricomet

LinkedIn : https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/mycompany/

Instagram: https://instagram.com/safaricomet

ተመሳስለው ከሚከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች ራሳችንን እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::