የኖርዌይ መንግስት ያወጣው የስራ ቅጥር እድል በሚል በተለይ ዋትሳፕ ላይ እየተሰራጨ ያለ ማጭበርበርያ!

ከሰሞኑ በምስሉ ላይ የሚታየው የኖርዌይ መንግስት ለዘንድሮ አመት ያወጣው የስራ ቅጥር እድል በሚል በተለይ ዋትሳፕ ላይ እየተሰራጨ ያለ የማጭበርበርያ መልዕክት እንዳለ ተመልክተናል።

አሳሳች መልዕክቱ ኖርዌይ በዚህ አመት 380,000 ሰው ለስራ እንደምትፈልህ ይገልፅና ከዚህ ውስጥ ለ120,000 ያህሉ አሁን ማመልከቻ ማስገባት እንደሚቻል ይጠቁማል።

እንዲህ አይነት መልዕክቶችን የሚያሰራጩ ግለሰቦች በአብዛኛው በውጭ ሀገር የሚገኙ ሲሆን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ከግለሰቦች ገንዘብ ተቀብለው ይጠፋሉ። ለቪዛ ፕሮሰስ ማድረጊያ፣ ለጠበቃ መቅጠርያ፣ ለቀጠሮ ማስያዣ እና ሌሎች ምክንያቶችን ደጋግመው ሲጠቀሙ ይታያል።

ይህ መልዕክት የኖርዌይ መንግስት ኦፊሴላዊ ድረ-ገፆች ላይ የሌለ ሲሆን በዋናነት በዋትሳፕ አማካኝነት የተሰራጨ ነው። የሚያገኙት ሊንክ ትክክለኛ መሆኑን ሳያረጋግጡ ምንም አይነት የመልዕክት ልውውጥ አያድርጉ፣ ክፍያም አይፈፅሙ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::