በፎቶ ቅንብር ተቀይሮ ማህበራዊ ሚድያ ላይ የተጋራ ምስል! 

ከ16 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ‘’ታደለ ሲሳይ – Tadele Sisay’’ የሚል መጠርያ ያለው የፌስቡክ ገጽ “በጎንደሩ ግጭት አጥፊዎቹ እኛው ሙስሊሞች ነን!” የሚል መፈክር የያዘ ሰው ፎቶ ማጋራቱን ተመልክተናል። ይህ ፎቶም ከ1 ሺህ በላይ ላይክ እና ከ350 በላይ ሼር አግኝቷል። 

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ የፎቶፎረንሲክ እና የሪቨርስ ፎቶ መፈለጊያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት በፎቶው ላይ የሚነበበው ጽሁፍ መነካካቱን ወይም መለወጡን አረጋግጧል። 

ትክክለኛው ፎቶ ከ269 ሺህ በላይ በላይ ተከታዮች ባሉትና ‘’Mujib Amino’’ የሚል ስያሜ ባለው የፌስቡክ ገጽ የተጋራ ነው። በትክክለኛ ፎቶም “እምነታችን ሩሃችን፤ ትምህርታችን አካላችን ነው!” የሚል ጽሁፍ ይነበባል። የፌስቡክ ገጹ ባለቤት ፎቶውን የፕሮፋይል ምስል በማድረግ እንደሚጠቀምበትም ተመልክተናል።

ማህበራዊ ሚድያ ላይ የሚሰራጩ መረጃዎች፣ ምስሎች እና ቪድዮዎች በሙሉ ትክክለኛ ስላልሆኑ ለሌሎች ከማጋራታችን በፊት ቆም ብለን እናስብ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::