በአቶ በላይነህ ክንዴ ስም እና ምስል ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆች!

የታዋቂውን ባለሃብት አቶ በላይነህ ክንዴን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች መኖራቸውን ተመልክተናል። ከገጾቹ መካከል ከቀናት በፊት የተከፈተና ከ5 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት “Belayneh Kindie-በላይነህ ክንዴ” የሚል ስም የሚጠቀም ይገኝበታል።

በገጹ ላይ በብር የሚመነዘሩ ቻሌንጆች ተለጥፈው የተመለከትን ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ግብረመልሶችን መስጠታቸውን አስተውለናል።

ኢትዮጵያ ቼክ የገጾችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አቶ በላይነህ ክንዴን ያነጋገረ ሲሆን ምንም አይነት የፌስቡክ አካውንት እንደሌላቸውና በገጾቹ የሚለጠፉ መልዕክቶችም የሳቸው አለመሆናቸውን አስታውቀዋል።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::