“መረጃው የተሳሳተ ነው”— የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ቼክ

ከ173 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግዕዝ ሚዲያን ጨምሮ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በቀይ መስቀል በኩል እንዲወጡ እንደሚደረግ የሚገልጹ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ተመልክተናል። 

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከላይ የተጠቀሰው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ዛሬ ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቋል።  

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል መረጃው የተሳሳተ መሆኑን ገልጸው ወላጆችና ህብረተሰቡ የሚመለከታቸው አካላት ብቻ የሚሰጡትን መረጃ እንዲከታተሉ መክረዋል። 

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትናንት ምሽት በሰጠው መግለጫ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎችን በተመለከ  ከተለያዩ አካላት፣ የየዩኒቨርስቲዎቹ አመራሮች እና ከዓለም አቀፍ ተራድኦ ተቋማት ጋር በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ መግለጹ ይታወቃል።  

ከዩኒቨርስቲዎች አመራር ጋር መገናኘት መቻሉንና ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ማወቅ መቻሉን መግለጹም ይታወቃል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::