በጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

ስም እና ምስል ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶች! 

የጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ስም እና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ በርካታ የፌስቡክ ገጾች እና አካውንቶች እንደሚገኙ አስተውለናል። እነዚህ በምስሉ ላይ የሚታዩት ሁሉ የእርሱ አለመሆናቸውን ጋዜጠኛ መሳይ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል። 

በነዚህ ሀሰተኛ ገጾች አንዳንድ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች ጭምር እየተላለፉ ይገኛል፣ በርካቶች ደግሞ እውነት መስሏቸው እያጋሩት ይገኛል። 

ጋዜጠኛ መሳይ እነዚህ ገፆች ሀሰተኛ መሆናቸውን ለኢትዮጵያ ቼክ የገለፀ ሲሆን ትክክለኛው አካውንቱ ይህ እንደሆነ ጠቁማል: https://www.facebook.com/mesay.mekonnen.7 

ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾችን እና አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እራሳችንን እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::