“የሉሲፈር ምዝገባ” በማለት በፌስቡክ እና ቴሌግራም እየተደረገ ያለ የማጭበርበር ድርጊት ሲጋለጥ! 

“የታላቁ ሉሲፈር (ሰይጣን) ምዝገባ” በሚል ርዕስ በርካታ ሰዎችን የማጭበርበር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ማረጋገጥ ችሏል። ይህ የማጭበርበርያ ዘዴ “እንኳን ወደ ኢሊሙናትየም የምዝገባ ማዕከል በደህና መጡ” ካለ በሗላ የተለያዩ አጓጊ ክፍያዎችን ቃል በመግባት የሚፈፀም ነው። 

“አዲስ ለሚመጣ አባል የሚሰጡ ጥቅሞች” በማለት 500,000 ብር የመጀመሪያ ክፍያ ከዛም በየስድስት ወሩ ይከፈላል ይላል። በተጨማሪም “ማጂክ ሪንግ ቀለበት፣ የእጅ የወርቅ ሰአት እና በመረጡበት ቀን የ 6 ቀን የፓሪስና ግሪክ ጉብኝት” እንደሚያመቻቹ ይገልፃሉ። 

ኢትዮጵያ ቼክም አንዱን የድርጊቱን ተባባሪ ተመዝጋቢ በመምሰል ቀርቦ በምስሉ ላይ የሚታየውን መረጃ አግኝቷል። በዚህም መሰረት “ተከታዮች ማፍራት እና ደንበኞችን ሚሊየነር ማድረግ” አላማቸው እንደሆነ የሚናገሩ ሲሆን ከዝቅተኛው 3,000 ብር ጀምሮ ለምዝገባ በመቀበል ከዛም እንደሚሰወሩ ለማወቅ ተችሏል። 

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ተከታታይ ማጣራት ስማቸው እዚህ የተዘረዘሩ ግለሰቦች የድርጊቱ ተሳታፊ መሆናቸውን ተመልክቷል፣ የበርካቶቹንም ስልክ ቁጥር ለመያዝ ችሏል: 

Alemayehu Tessema, Eyoba Man, Yonatal Arefayine, Kassahun Melike, Sufiyaan Bashir, Eyob Endayfer, Ahmedin Husen Deedaat, Getahun Zelalem, Mesele Abute, Yonathan Mt, Mekonnen Aynayehu. 

የሚጠቀሙባቸው ስልክ ቁጥሮች: 

+251969079206

+251920656229

+251922268799

+261962876021

+251975146238

+14342802585 

ማህበረሰቡ ከእንዲህ አይነቱ “ሚሊየነር እናረጋችሗለን” ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሱን እንዲጠብቅ እያሳሰብን የህግ አካላትም በዚህ ድርጊት ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ወደ ፍትህ እንዲያቀርቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::