ትክክለኛው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት የፌስቡክ ገፅ!

በቅርብ ሳምንታት ስራ የጀመረው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት የተለያዩ መረጃዎችን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሚድያ አካላት እያቀረበ መሆኑ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የአገልግሎቱ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅን አጣርተን እንድናሳወቅ ጥያቄዎች ደርሰውናል።

በመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ትክክለኛው የአገልግሎቱ የፌስቡክ ገፅ ይህ እንደሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል (https://www.facebook.com/FDRECommunicationService/)።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::