ይህ ትክክለኛ የአርቲስት ታማኝ በየነ የትዊተር አካውንት ነው?

ይህ የአርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነን ስምና ፎቶግራፍ በመጠቀም የተከፈተና ከ2,000 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት ትክክለኛ ስለመሆኑ በርከት ያሉ ሰዎች ጥያቄ ሲጠይቁ ተመልክተናል።

እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም የተከፈተው ይህ የትዊተር አካውንት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተከታታይ መልዕክቶችን ሲያጋራና በርከት ያለ ግብረመልስ ሲያገኝም አስተውለናል። ባለፈው 24 ሰአት ብቻ ከ 500 በላይ አዲስ ተከታይም አግኝቷል።

ኢትዮጵያ ቼክ የአካውንቱን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አርቲስቱን ያነጋገረ ሲሆን፣ አካውንቱ የእርሱ አለመሆኑን አስታውቋል።

በዚሁ አርቲስት ታማኝ የሚጠቀምበትን የፌስቡክ ገፅ እንጠቁማችሁ: https://www.facebook.com/ArtistTamagne/

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::