ይህ የምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሌተናል ጀኔራል አበባው ታደሰ የፌስቡክ ገጽ ነው?

ይህ ከ56 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት በጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሌተናል ጀኔራል አበባው ታደሰ ስም የተከፈተ የፌስቡክ ገጽ ሀሰተኛ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ከወራት በፊት ማጋለጡ ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ቼክ የገጹን ሀሰተኛነት ካጋለጠ በኃላ ስሙ ወደ ‘Ethiopia Today’ ተቀየሮ ቆይቷል። ከጥቂት ቀናት በፊት የገጹ ስም እንደገና ወደ ‘ሌ/ጀ አበባው ታደሰ’ መቀየሩን አስተውለናል። ገጹ የሌተናል ጀኔራል አበባው ታደሰ አለመሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾችን እና አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እራስዎን ይጠብቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::