ይህ ምስል ትክክለኛ ነው? 

ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የቀድሞው የኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ እና የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሉላ ሰለሞን አንድ መድረክ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠው የሚያሳይ ምስል ሲዘዋወር አስተውለናል። 

ምስሉ የተነካካ (ፎቶሾፕ የተደረገ) ለመሆኑ በቂ ምልክቶች እንዳሉት በፎረንሲክ መሳሪያዎች ማጣራት ችለናል። የሁለቱ ግለሰቦች ፎቶም ከዚህ በፊት በተለያዩ የህትመት እና የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች እንደተጋሩም ለማረጋገጥ ችለናል። 

የአቶ ታምራት ላይኔ ምስል ነሀሴ 15፣ 2011 በአንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ የተጋራ የቆየ ፎቶ መሆኑን አረጋገጠናል (ምስሉ ከታች ተያይዟል)። ይህንኑ ምስል በአግድም በመገልበጥ (mirroring) እና ምስሉን በቀይ መስመር ምልክት ባደረግንበት ቦታ ላይ በመቁረጥ (cropping) ለማስተካከል ሙከራ እንደተረገም እንዲሁ ማረጋገጥ ችለናል። 

በዚህም መሰረት ምስሉ በቅንብር የቀረበ እንደሆነ ማየት እንችላለን። 

አሳሳች እና የተነካኩ ምስሎችን ባለመጠቀም ለሀሰተኛ መረጃ መቀነስ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበርክት።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::