ይህ የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ትዊተር አካውንት ነው?

ይህ የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻን ስምና ፎቶግራፍ በመጠቀም በያዝነው ወር የተከፈተና ከ740 በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት ትክክለኛ ስለመሆኑ በርከት ያሉ ሰዎች ጥያቄ ሲጠይቁ ተመልክተናል።

አካውንቱ በትናትናው ዕለት እና ዛሬ ብቻ በርከት ያሉ ገደማ ትዊቶችን ያጋራ ሲሆን አንዳንዴም በሺዎች የሚቆጠር በርከት ያለ ግብረ-መልስም (reaction) ሲያገኝ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ የአካውንቱን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ጋዜጠኛ አስፋውን ያነጋገረ ሲሆን፣ አካውንቱ የእርሱ አለመሆኑን አስታውቋል።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡና ሀሠተኛ
ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::