ይህ የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት የአቶ ለማ መገርሳ የፌስቡክ ገጽ ነው?

የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር በነበሩት በአቶ ለማ መገርሳ ስም እና ምስል የተከፈቱ በርካታ የፌስቡክ አካውንቶች ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች አቶ ለማ የፌስቡክ አካውንት እንዳላቸው እንድናጣራ በጠየቁን መሰረት ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር።

አቶ ለማ የፌስቡክ አካውንትም ሆነ ገፅ እንደሌላቸው ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድተዋል።

ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆችን ባለመከተል የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ይከላከሉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::