ይህ የቢቢሲ አማርኛ ትክክለኛ ገጽ ነው?

እ.ኤ.አ. አፕሪል 2021 የተከፈተ እና ከ21 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የቢቢሲ አማርኛን ስም እና አርማ በመያዝ የተለያዩ ዜናዎችን ይህ ገጽ ሲያሰራጭ ተመልክተናል። ገጹ የሚያሰራጫቸው ዜናዎች የቢቢሲ ዜናዎችን ጨምሮ የሌሎች የዜና አውታሮችን ያካተተ መሆኑንም ታዝበናል።

የዚህን ገጽ ትክክለኛነት ለማጣራትም የቢቢሲ የአማርኛ ቋንቋ ክፍል ባልደረቦችን አግኝተን መረጃ አግኝተናል፣ በዚህም መሰረት ይህ ገጽ ሀሰተኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል።

“ይህ አካውንት ከእኛ የአማርኛ አገልግሎት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለውም” ብለውናል። አክለውም “ትክክለኛው የቢቢሲ የአማርኛ ቋንቋ ገጽ BBC News Amharic የሚል ሲሆን በእንግሊዝኛ የተጻፈ እና የተረጋገጠ አካውንት (verified account) መሆኑን የሚያሳየው ሰማያዊ ምልክት እንዳለውም ልብ ማለት ይገባል” ብለዋል።

በተያያዘም በቢቢሲ ስም ዜናዎችን ይዘው የሚቀርቡ የቴሌግራም ቻናሎች መኖራቸውን መታዘባችንን እና ይህንንም እንዲያረጋግጡልን በጠየቅናቸው መሰረት፣ ይህ ጽሁፍ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ቢቢሲ በአማርኛም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ዜናዎችን የሚያሰራጭበት የቴሌግራም ቻናሎች እንደሌሉት አረጋግጠውልናል።

የቢቢሲ አማርኛ ትክክለኛው ገጽ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው:

https://www.facebook.com/BBCnewsAmharic

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::