በደብረ ማርቆስ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል?

“ሰበር ዜና” በማለት በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ ተብሎ ፌስቡክ ላይ የተሰራጨው መረጃ “ሀሠት” ነው ብሎ የከተማው አስተዳደር ፖሊስ ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ሃላፊ ኮማንደር ዮሃንስ በየነ ለኢትዮጵያ ቼክ በስልክ እንደገለፁት የሰዐት እላፊ ገደብ ተጣለ ተብሎ የተጋራው መረጃ “ሃሰት” ነው።

የከተማው ፖሊስ በማህበራዊ ሚድያ ገፁ ከደቂቃዎች በፊት እንደገለፀው “ምንም አይነት የተለየ እንቅስቃሴን ሊገድብ የሚችል የፀጥታ ችግርም ሆነ ስጋት በከተማው የለም” ያለ ሲሆን መረጃውን ያጋሩት “የማርቆስ ሰላም የማይዋጥላቸው” ያላቸው አካላት እንደሆነ ጠቅሷል።

ፖሊስ አክሎም በከተማው ውስጥ ምንም የጸጥታ ስጋት የሌለ እና አመታዊ የማርቆስ በአልን ለማክበር ህብረተሰቡ፣ ወጣቶች እና የጸጥታ ሀይሉ አስፈላጊ የሰላም ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ ብሏል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::