ለወላይታ ሶዶ አየር ማረፊያ ግንባታ ጨረታ ወጥቷል? 

“Melese Dlk” የተባሉ ተከታታያችን “በወላይታ ሶዶ የአየር ማረፍያ ግንባታ ለማሰራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጨረታ አውጥቷል የሚሉ በአንድ በኩል፣ በሌላ በኩል አላወጣም ፌክ post ነው የሚሉ አሉና እውነቱ check ቢደረግ” የሚል ጥያቄ ልከውልናል። 

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ በአየር መንገዱ የወጡ የጨረታ መረጃዎችን አግኝቷል። 

በዚህም መሰረት አየር መንገዱ ደረጃ 3 እና ከዛ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ወይም የመንገድ ስራ ተቋራጭ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሶዶ አየር ማረፊያን በዲዛይና ግንባታ የውለታ አይነት ማሰራት እንደሚፈልግ ማስታወቁን አይተናል። 

ጨረታውም በጨረታ ቁጥር -SSNT-T241 ስር በድርጅቱ ድህረ ገፅ(corporate.ethiopianairlines.com) ላይ ይገኛል። 

ስለዚህ በዚህ ዙርያ ጨረታ እንደወጣ ማረጋገጥ ተችሏል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::