የደቡብ ሱዳን የውሀና መስኖ ሚኒስትር በግብፅ “ጉብኝት” ላይ እያሉ ህይወታቸው ማለፉ ትክክለኛ መረጃ ነው?

ሚኒስትሩ ማናዋ ፒተር ጋትኩኦት ህይወታቸው ማለፉ በትናንትናው እለት ይፋ ከተደረገ በኋላ በርካታ መላምቶች ሲዘዋወሩ ተመልክተናል፣ አንደኛው ደግሞ ሚኒስትሩ ህይወታቸው ያለፈው “ጉብኝት” ላይ እንደሆነ ይጠቅሳል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ መረጃዎችን ያሰባሰበ ሲሆን የደቡብ ሱዳኑ ሚኒስትር ህይወታቸው ያለፈው በከፍተኛ የደም ግፊት ምክንያት ለህክምና ወደ ግብፅ ካመሩ በኋላ መሆኑን ማየት ችለናል።

Eye Radio የተባለው የሀገሪቱ ሚድያ የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቻርን ጠቅሶ እንደፃፈው ማናዋ ፒተር ጋትኩኦት ካይሮ ውስጥ ህይወታቸው ያለፈው በፍሪደም እና ባርካ ሆስፒታል ውስጥ ነበር፣ ወደ ግብፅ ለህክምና የተወሰዱትም በአስቸኳይ በረራ ነበር።

ስለዚህ የሚኒስትሩ ህልፈት ትክክለኛ ቢሆንም ህልፈታቸው በጉብኝት ላይ እንደነበር የተገለፀው የተሳሳተ ስለሆነ መረጃውን ቅይጥ ያደርገዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::