“የኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ” ወይስ “ከአለም ምርጥ ባንኮች አንዱ”?

በትናንትናው እለት አዋሽ ባንክ በግሎባል ፋይናንስ መፅሄት እውቅና እንዳገኘ በስፋት ተዘግቧል። የሀብት እድገት፣ ትርፋማነት እና ተደራሽነት ላገኘው እውቅና ምክንያቶች እንደሆኑም ተገልጿል።

ፋና እና ዋልታ ባንኩ “በኢትዮጵያ ምርጡ ባንክ” ተብሎ እንደተመረጠ ሲዘግቡ እንደ ኢቢሲ፣ ደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቭዥን፣ የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት፣ ሸገር ኤፍኤም እንዲሁም ራሱ ባንኩ (በፌስቡክ ገፁ) “ከአለም ምርጥ ባንኮች አንዱ” ሆኖ እንደተመረጠ መረጃ አቅርበዋል።

መፅሄቱ ያወጣውን መረጃ የተመለከተ ማንኛውም ሰው ማየት እንደሚችለው አዋሽ ባንክ የተመረጠው በኢትዮጵያ ካሉ ባንኮች ምርጡ ተብሎ ነው: https://d2tyltutevw8th.cloudfront.net/media/document/worlds-best-banks-2022-africa-1648498404.pdf

በዚህም መሰረት የፋና እና ዋልታ ዘገባ ትክክለኛ ሲሆን በኢቢሲ እና ሎሎቹ ሚድያዎች “ከአለም ምርጥ ባንኮች አንዱ” ተብሎ የቀረበው የተሳሳተ ነው።

መፅሄቱ በአለም ምርጥ የኢንቨስትመንት ባንኮች ዝርዝር አውጥቷል፣ አዋሽ ባንክ ግን የኮሜርሺያል እንጂ የኢንቨስትመንት ባንክ ስላልሆነ እዚህ ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም።

ይህ ለሚድያዎች ምን ትምህርት ይሆናል? የቢዝነስ ተቋማትም ሆነ ድርጅቶች ያሉትን በቀጥታ ገልብጦ ከመዘገብ ይልቅ የመረጃው ምንጭ ወደሆነው አካል ሄዶ ማጣራት እንዲህ አይነት ስህተትን ለማስቀረት ይረዳል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::