አሜሪካ ዜግነት የሌላቸውን ኢትዮጵያዊንን ከሀገሯ ልታስወጣ ነው?

“Wolkayt Tegedie Amhara Revolution” የተባለ 88,000 በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ከሁለት ቀን በፊትሰበር  ዜናበማለት የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አሜሪካዊ ዜግነት የሌላቸውን ማንኛውም ኢትዮጵያዊያንከአገሯ እንዲወጡላት የሚያዝ ረቂቅ ማዘጋጀቷን አስነብቧል።

ገፁ አክሎም “[ረቂቁ] ለሕዝብ መወሰኛው የላይኛው ምክር ቤት መቅረቡን አንድ የአሜሪካን የፓርላማ ምክርቤት አባል መናገራቸው በሰፊው እየተዘገበ ነውብሎ መረጃ አጋርቷል። ይህምሰሞኑን በተፈጠረው የኢትዮጵያመንግሥት ቅስቀሳ የአሜሪካን ባንዴራን እናቃጥላለን ማለታቸውን ተከትሎ ነውብሏል።

ይህ መረጃ በማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት የተሰራጨ ሲሆን በርካታ ተከታታዮቻችንም መረጃውንእንድናጣራላቸው ጥያቄ አቅርበውልናል።

ይህን መረጃ ለማጣራት በመረጃው ላይ የተጠቀሰውን እና ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይቢሮ (State Department) ኢትዮጵያ ቼክ አናግሯል።

ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ቢሮ ቃል አቀባይ ቢሮ በቀጥታ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከላይ በተጠቀሰውየፌስቡክ ገፅ የተላለፈው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

የቃል አቀባይ ቢሮው በሰጠን መልስእነዚህ ግርምትን የሚጭሩ የኦንላይን ሪፖርቶች ሙሉ በሙሉ የሀሰትናቸው። እንዲህ አይነት የሀሰተኛ መረጃዎች በኢትዮጵያ ያለውን ችግር ከማባባስ የዘለለ ፋይዳ የላቸውምብሏል።

አሜሪካ በኢትዮጵያና በኤርትራ ባለስልጣናት በወታደራዊና የደህንነት ሹማምንት፣ በአማራ ክልል አስተዳደርናየፀጥታ መዋቅር መሪዎች እንዲሁም በወንጀል የተሳተፉ የሕወሓት መሪዎች ላይ የጉዞ ማዕቀብ መጣሏ በስፋትተዘግቧል።

ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካእርምጃንየተሳሳተእንደሆነ ገልፆ በፅኑ አውግዟል። /ቤቱ አክሎምይህ እርምጃ ለዘመናት ፀንቶ የቆየውንየሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን ሊያጠለሽ የሚችል ነው፣ አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ ጣልቃ ለመግባትየሚሞክሩ አካላትን አትቀበልምብሏል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::