አማዞን 27ኛ የምስረታ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ነጻ ስጦታዎችን ለእድለኞች እየሰጠ ነው? 

አማዞን (Amazon) የተባለው ኩባንያ 27ኛ የምስረታ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ ነጻ ስጦታዎችን ለእድለኞች እየሰጠ መሆኑን የሚያስተዋውቁ መልዕክቶች በፌስቡክ ሜሴንጀር (Facebook Messenger) በኩል ከደረሰዎ ለማጭበርበር የተላኩ መልዕክቶች ስለሆኑ መልዕክቱን እንዲያጠፉ እንመክራለን። 

ማረጋገጥ እንደቻልነው እርግጥ አማዞን ከተመሰረተ 27ኛ ዓመቱ ነው፣ ይሁንና ጭራሽ 27ኛ አመቱን እያከበረ አይደለም። 

እ.ኤ.አ. በ1994 የተመሰረተው ይህ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከተመሰረተ 27 ዓመት የሞላው ሲሆን የምስረታ ዓመቱን በማስመልከት ግን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ እያከበረ አይደለም። 

ነገር ግን በተላከው መልዕክት ላይ ያለውን አገናኝ (ሊንክ) ሲከተሉ የሚያገኙት የመጠይቅ ገጽ (survey) የአማዞን ሳይሆን ከአማዞን ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎ የተሰራ ገጽ ነው። ይህንን ለማረጋገጥ የአድራሻ መጻፊያው ላይ ያለውን የቃላት አጻጻፍ ስህተት ብቻ መመልከት በቂ ነው። 

ትክክለኛው የአማዞን ድር ጣቢያ በእንግሊዝኛው ‘Amazon’ የሚል ሲሆን ለማታለል የተቀሙበት ይህ ጣቢያ ግን ‘Amazsocn’ በሚል የሚጀምር አድራሻን የያዘ ነው። 

ለማታለል ወደተከፈቱ ገጾች መግባት እና እዚያ ላይ የሚገኙትን መጠይቆች መሙላት፣ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እንዳይሞክሩት እንመክራለን።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::