አርቲስት ታሪኩ ጋንካሲ መታሰሩን በመግለፅ የተሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው!

“ድሽታ ግና” በሚለው የሙዚቃ ስራው የሚታወቀው አርቲስት ታሪኩ ጋንካሲ ከቀናት በፊት በደቡብ ኦሞ ዞን ጅንካ ከተማና አካባቢው ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ስለመታሰሩ የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አርቲስት ታሪኩን ያነጋገረ ሲሆን የተሰራጨው መረጃ “ውሸት” መሆኑንና አለመታሰሩን አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስን ያነጋገረ ሲሆን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ሻለቃ ዮሃንስ አርቲስት ታሪኩ አለመታሰሩን አረጋግጠዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን የአሪ ብሔአሰብ በዞን የመደራጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከቀናት በፊት በዞኑ ዋና ከተማ ጅንካና አካባቢው በተፈጠረ ሁከት በሰዎች ላይ እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ በተለያየዩ ሚዲያዎች መዘገቡ ይታወቃል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::