አትሌት ሰለሞን ባረጋ ከኦሎምፒክ ድል መልስ ከተበረከቱለት ሽልማቶች ጋር ተያይዞ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በወጡት መረጃዎች ዙርያ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ አካፍሏል!

በቶክዮ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ ያስገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋን የተመለከቱ አንዳንድ መረጃዎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጩ ይገኛሉ።

መረጃዎቹ አትሌቱ ከኦሎምፒክ መልስ የተሸለመው መኪና እስካሁን እጁ እንዳልገባ እንዲሁም የደቡብ ክልል ወልቂጤ ከተማ ላይ የሸለመው 10 ሺህ ካ.ሜ. መሬት እስካሁን እንዳላስረከበው ይገልፃሉ።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ከአትሌቱ ጋር ዛሬ አጭር ቃለ-መጠይቅ አርጎ ነበር፣ ዝርዝሩ ይህን ይመስላል:

በመኪናው ዙርያ: “የሽልማት መኪናውን የሚያስመጣው ሞኤንኮ ነበር። ይሁንና ሀገሪቱ ካጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር ተያይዞ ድርጅቱ ይህን ማግኘት አልቻለም፣ በዚህ መሀል ብዙ ሙከራዎች ሲደረጉልኝ ነበር። ከፈለግህ የመኪናውን ዋጋ የሚያወጣ ገንዘብ እንስጥህ ተብዬ ነበር፣ እኔ ስላልፈለግኩ ነው። አሁን ግን በራሴ ውጭ ምንዛሬ ሌላ አይነት ምርጫዬ የሆነ መኪና ከቀረጥ ነፃ ሆኖ እንዲገባልኝ ለገንዘብ ሚኒስቴር ደብዳቤ አስገብቻለሁ። አሁን እሱን እየተጠባበቅኩ እገኛለሁ።”

በመሬቱ ዙርያ: “መሬቱ እስካሁን እጄ ያልገባው በስፖርት ኮሚሽን የአመራሮች ለውጥ ስለነበር ነው። መሬቱን በዚህ ሳምንት እንደሚያስረክቡኝ ነግረውኛል። ስራ ስለሚበዛብኝ የመሬቱን ጉዳይ እኔ በግሌ መከታተል አልቻልኩም ነበር፣ አሁን ግን እያወራን ነው። በአጠቃላይ ከኦሎምፒክ ስመለስ በተሰጡኝ ሽልማቶች ዙርያ ማህበራዊ ሚድያ ላይ የወጡት መረጃዎች እኔ ያልተናገርኳቸው ናቸው።”

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::