“ዜግነቴን መቀየር ብፈልግ እኔ በግልጽ እናገር ነበር፣ የቀየርኩት ዜግነት የለም፣ ለመቀየረም ምክንያት የለኝም፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ”— አትሌት ሙክታር እድሪስ ለኢትዮጵያ ቼክ

“4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ” የሚል ስያሜ ያለውና ከ128 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ “ኢትዮጵያን በአለም እና በኦሎምፒክ መድረክ ላይ በ5 እና 10 ሺህ ሜትር ወክሎ በመወዳደር በተደጋጋሚ ለሀገራችን የወርቅ መሰል ውጤቶችን ሲያስመዘግብ የነበረው ከደቡብ ክልል ስልጤ ዞን የተገኘው አትሌት ሙክታር እድሪስ ዜግነቱን ወደ ቱርክ ቀይሯል። ምን እየተሰራ ይሆን?” የሚል መልዕክት አጋርቶ ነበር።

ገጹ መልዕክቱን ከሰዐታት በኃላ ቢያጠፋውም መረጃው በስፋት መሰራጨቱን ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን ለማጣራት አትሌት ሙክታር እድሪስን ያነጋገረ ሲሆን የተሰራጨው መረጃ ሀሠተኛ መሆኑን አስታውቋል። “እንደዚህ አይነት ሀሠተኛ መረጃ ለምን ማሰራጨት እንደፈለጉ አልገባኝም፣ ዜግነቴን መቀየር ብፈልግ እኔ በግልጽ እናገር ነበር፣ የቀየርኩት ዜግነት የለም፣ ለመቀየረም ምክን ያት የለኝም፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ። አሁን ያለሁትም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው” በማለት ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድቷል።

አትሌት ሙክታር እድሪስ በአለም ሻምፒዮና ለሁለት ተከታታይ ጊዜ በ5 ሺህ ሜትር ለሀገሩ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱ ይታወቃል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::