የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) አዲስ የፌስቡክ አካውንት ከፍቷል?

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባለፈው ሰኞ የጠለፋ (hacking) ሰለባ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል፣ ከዛ ወዲህ ለሰአታት ተመልሶ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ከነጭራሹ ገፁ አይታይም። 

ይህንን ተከትሎ በርካታ መላ ምቶች እየተሰነዘሩ ሲሆን ለምሳሌ አንዳንድ አክቲቪስቶች ተቋሙ በምስሉ ላይ የሚታየውን አዲስ የፌስቡክ ገፅ እንደከፈተ ፅፈው ተመልክተናል፣ የገፁን ሊንክም በስፋት ሲያጋሩት ተስተውለዋል። 

ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ዙርያ ማጣራት ያደረገ ሲሆን በምስሉ ላይ የሚታየው ተመሳስሎ የተከፈተ ገፅ መሆኑን አረጋግጧል። 

ከ2.2 ሚልዮን በላይ ተከታይ የነበረው እና የፌስቡክ ማረጋገጫ ያለው የተቋሙ ኦፊሴላዊ ገፅ ከጠለፋው ወዲህ አሁን ምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ኢትዮጵያ ቼክ መረጃው ካላቸው ምንጮች ጠይቋል። ያገኘው መልስም “ገፁ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እና የማጠናከርያ ስርዐቶች ተዘርግተው እስኪያልቁ አሁን ኦንላይን ላይ እንዳይገኝ ተደርጓል” ይላል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::