ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሰሞኑ በሰሜን ኮርያ ጉብኝት አርገው ነበር?

በምስሉ ላይ እንደሚታየው በዛ ያሉ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች እና አካውንቶች ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከሰሞኑ በሰሜን ኮርያ ጉብኝት እንዳካሄዱ ወይም እያካሄዱ እንደሆነ ፅፈዋል፣ አሁንም እየፃፉ ይገኛሉ። በዚህ ዙርያ የወጣውን መረጃ እንድናጣራም በርከት ያሉ መልዕክቶች ደርሰውናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑትን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንን ዛሬ ማሻውን ያናገረ ሲሆን መረጃው የሀሰት እንደሆነ አረጋግጠዋል።

“ምንጩ ከየት እንደሆነ የማይታወቅ ተራ ግምት መሆን አለበት” ብለው የተሰራጨውን መረጃ ሀሰትነት በአጭሩ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ ከተሳሳተው መረጃ ጋር አብረው የቀረቡ ምስሎች ላይም ማጣራት ያረገ ሲሆን ምስሎቹ የሚያሳዩት ጠ/ሚሩ የዛሬ ሁለት አመት ገደማ በደቡብ ኮርያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተነሳውን ነው።

በተጨማሪም ጠ/ሚሩ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት እና ልዑካቸውን መቀበላቸው የዚህ የተሳሳተ መረጃን ያጋለጠ ሆኗል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::