አሳሳቹ የትዊተር አካውንት: ከጆርጅ ቦልተን ወደ ጆን ዊልደር?

ያሳለፍነው ማክሰኞ እለት የኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት እና ዋልታ “ጆርጅ ቦልተን” ከሚል ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት መረጃ ወስደው እንዳጋሩ እንዲሁም በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች መረጃውን ሲቀባበሉ እንደነበር ኢትዮጵያ ቼክ አሳውቆ ነበር።

በዜናዎቹም “የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ሽግግር ያደናቅፋል” ብለው እኚህ ግለሰብ እንደተናገሩ እነዚህ ሁለት ሚድያዎች ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ በወቅቱ በጆርጅ ቦልተን የትዊተር አካውንት ላይ ባደረገው ማጣራት የፕሮፋይል ምስሉ (profile picture) የረቀቀ የማስመሰል ጥበብን (deep fake) በመጠቀም የተሰራ ሀሰተኛ ፎቶ መሆኑንን አረጋግጦ ነበር።

አሁን ላይ ከአካውንቱ መመልከት እንደቻልነው የዚህ የትዊተር አካውንት የፕሮፋይል ፎቶው በሌላ ተቀይሯል፣ ይሁንና አሁንም የተቀየረው ፎቶ የአሜሪካዋ ግዛት ቴነሲ 43ኛ ገዢ በነበሩት ጆን ዊልደር ነው። ፎቷቸው በዚህ አሳሳች የትዊተር አካውንት ላይ በአዲስ መልክ የተቀመጠው ጆን ዊልደር የ93 አመት አዛውንት ናቸው።

አሳሳች እና ተመሳስለው የሚከፈቱ አካውንቶችን፣ ገፆችን እና ቻናሎችን ባለመከተል የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ይከላከሉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::