ለጥንቃቄ! 

በርከት ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች “የኮካ ኮላ ደህነት ፈንድ” የሚል ማስፈንጠሪያ (link) በፌስቡክ ሜሴንጀር እንዲሁም በኢሜል አድራሻቸው በተደጋጋሚ እንደደረሳቸው ሲገልጹ ተመልክተናል። ክስተቱ በኢትዮጵያ ብቻ ሳያሆን በሌሎች ሀገሮችም ስለመስተዋሉ ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው የማህበራዊ ሚዲያ ዳሰሳ አስተውሏል። 

በኢትዮጵያ የተሰራጩ መልዕክቶች “እንኳን ደስ አላችሁ” በሚል የግብዣ ርዕስ የሚጀምሩ ሲሆን “ዛሬ ሰኔ 6, 2021 ለዳሰሳ ጥናታችን በመመረጠው በጣም ዕድለኛ ነዎት። በአንድ ደቂቃ ውስጥ ብቻ አስደናቂ ሽልማት ታገኛለህ!” የሚል ፅሁፍ ይነበብባቸዋል። 

የኮካ ኮላ ኩባንያ እንዲሁም በርከት ባሉ ሀገሮች የሚገኙ የኮካ ኮላ ኩባንያ ቅርንጫፎች በድረገጻቸው እንዳስታወቁት በኮካ ኮላ ኩባንያ ስም እየተላኩ ያሉ እነዚህ ማስፈንጠሪያዎች ድርጅቱን የሚወክሉ አይደሉም። ከመልዕክቶቹ የሚያያዙት ማስፈንጠሪያዎች ወደ ድርጅቱ ኦፊሴላዊ ድረገጽ እደማያመሩም የኮካ ኮላ ኩባንያ ገልጿል። 

ከላይ የተገለጸውን አይነት መልዕክት በመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎች እና በኢሜል አድራሻዎ ከደረስዎ፣ ከአታላዮች የተላከ መሆኑን አውቀው ማስፈንጠሪያዎችን ከመክፈት ይቆጠቡ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::