ስለ ኮሜዲያን ልጅ ያሬድ እየተጋራ የሚገኝ ሀሰተኛ መረጃ!

ከጥቂት ሰዓታት ወዲህ በርካታ የፌስቡክ ገጾችና አካዉንቶች “ኮሜዲያን ልጅ ያሬድ ዛሬ ቡራዩ ላይ ማንነቱ ባልታወቀ ሰዉ በጥይት ተመቶ ተገደለ” በማለት መረጃዎችን እያጋሩ ይገኛሉ። 

 ለምሳሌ ያክል ጃኖ ሚዲያ የተሰኘና ከ130 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ መረጃዉን ካጋራ ከሰዓታት ቆይታ በሗላ ጽሁፉን ከገጹ አጥፍቶታል። የተለያዩ የቴሌግራም ቻነሎችም መረጃዉን አጋርተዋል።

 ኢትዮጵያ ቼክ በቀጥታ ልጅ ያሬድን ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ ለጊዜዉ ባይሳካም መረጃዉ ሀሰተኛ መሆኑን ለኮሜዲያኑ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች አረጋግጧል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::