ኬንያ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ላይ ቅሬታ አስገብታ እንደነበር ተደርጎ የቀረበው መረጃ የተሳሳተ ነው!

“Kahawa Tungu” የተባለ ድረገፅ እና 54 ሺህ በላይ ተከታታይ ያለው የፌስቡክ ገፁ አትሌት ለተሰንበት ግደይበኦሬጎን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ 10 ሺህ ሜትር ውድድር ባሸነፈችበት ወቅት ሁለተኛ የወጣችውኬንያዊቷ አትሌት ሄለን ኦቢሪንበክርን መትታለችበሚል ኬንያ ቅሬታዋን ለአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽንአስገብታ እንደነበር አንድ ፅሁፍ አስነብቧል።

ድረገፁ አክሎ ቅሬታው በአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽንተቀባይነት እንዳላገኘያትታል። መረጃውን ደግሞበርካታ ኬንያውያን እና የሀገሪቱ ጋዜጠኞች ሲያጋሩ ተመልክተናል።

ጉዳዩን በተመለከተ ኢትዮጵያ ቼክ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን የጠየቀ ሲሆንምንም አይነት ቅሬታአልቀረበምየሚል መልስ አግኝቷል። ቅሬታ ቀርቦ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽ የቴክኒክ ኮሚቴጋርም ይደርስ እንደነበር ታውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ የአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ ቼክ በላከው አጭር መልዕክትመረጃው የተሳሳተነውይላል። ቅሬታ እንደቀረበም ከዚህ ሚድያ ውጪ ሌሎች ሚድያዎች አልዘገቡትም።

በዚህ ምክንያት በዚህ የኬንያ ሚድያ የቀረበው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነ ማየት ይቻላል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::