በትግራይ ክልል ኢንተርኔት እና ስልክ ለደቂቃዎች ሰርቶ እንደነበር የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው!

አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ ገፆች እና አካውንቶች ባለፉት ጥቂት ቀናት፣ በተለይ ከትናንት በስቲያ በትግራይክልል 20 ደቂቃ ያህል ሞባይል ኔትወርክና ዳታ ለሙከራ ሰርቶ እንደነበር ሲፅፉ ተመልክተናል።

በነዚህ መረጃዎች መሰረት መንግስት የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎቶችን በትግራይ ክልል በድጋሜለማስጀመር የጀመረውን ስራ ጨርሶ ሙከራ እያረገ ይገኛል፣ በቅርብ ቀናትም ሙሉ በሙሉ ሊለቀቅ እንደሚችልይጠቁማሉ።

እነዚህ መልዕክቶች በርካታ ማጋራት፣ መውደድ እና አስተያየት ያገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችምየመረጃውን ትክክለኛነት እንድናጣራ ጥያቄ ሲያቀርቡልን ነበር።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ያለውን እውነት ለማጣራት በክልሉ የሚገኙ ሁለት ጋዜጠኞችን እና አንድ የረድኤት ድርጅት ባልደረባን አናግሯል። ሁሉም በተመሳሳይ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ቼክ ያሳወቁት መረጃውሀሰተኛመሆኑንነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሪፖርተር ጋዜጣ የዛሬ ወር ገደማ አንድ ምንጩን ጠቅሶ እንደፃፈው ስልክ፣ መብራት፣ ባንክእና ሌሎች አገልግሎቶች በትግራይ ክልል በቀጣይ ሳምንታት ሊጀመሩ እንደሚችሉ አስፍሮ ነበር። ከቀናት በፊትየአውሮፓ ህብረት በነበረው አንድ ስብሰባም እነዚህ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ ጥያዌ አቅርቦ ነበር።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::