በፕ/ር መረራ ጉዲና ዙርያ የወጣ ሀሰተኛ መረጃ!

‘UMD MEDIA’ የማህበራዊ ሚድያ ገፅ የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዋሽንግተን ዲሲ መሆናቸውን የሚገልጽ መልዕክት በትዊተርና በፌስቡክ ገጾቹ ለጥፏል። በተጨማሪም ፕሮፌሰሩ በመንግስት በረራ እንዳያደርጉ ተከልክለው እንደነበርና በአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ጉዞ ስለማድረጋቸው አስነብቧል። 

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ፕሮፌሰር መረራ በአሁኑ ሰዐት አዲስ አበባ እንደሚገኙ አረጋግጧል። ፕሮፌሰር መረራ ለኢትዮጵያቼክ እንደተናገሩት አሜሪካ ለመሄድ ሙከራ አላደረጉም፣ የአሜሪካ መንግስትም ጣልቃ አልገባም። 

ነገር ግን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አሜሪካ ለመሄድ ቪዛመውሰዳቸውን ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል። ወደ አሜሪካ የሚጓዙትም በዚያ ከሚገኙ የፓርቲያቸው አስተባባሪዎች ጋር ለመገናኘትና ገንዘብ ለማሰባሰብ ስለመሆኑ ለኢትዮጵያ ቼክ አስረድተዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::