የሀሰተኛ ምስል ማሳሰቢያ!

gemechu geleta’ በሚል ስም የተከፈተና ከ27,600 በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ባለቤት አምለሰት ሙጬ ክላሽንኮቭ በመባል የሚታወቀን የጦር መሳሪያ ይዛ ይታያል ያለውን ምስል አጋርቶ ነበር። 

ይህ ትዊት በርካታ መውደዶችን (like) እና መጋራት (retweet) ያገኘ ሲሆን ቁጥራቸው በዛ ያለ ሰዎችም አስተያየት ሰጥተውበታል። 

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው አካውንት ያጋራው ፎቶ የተነካካ (doctored) መሆኑን አረጋግጧል። 

ትክክለኛው ፎቶ አመለሰት ሙጬ የልጇን እጅ ስትስም የሚያሳይ ሲሆን እ.አ.አ ሚያዚያ 6/2019 ዓ.ም ከ893 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት የፌስቡክ ገጿ የተጋራ ነበር፣ ፎቶውን ኮራ ኢሜጅ እንዳነሳው የሚገልጽ መልዕክትም አብሮ ይታያል። 

አሳሳች፣ ከአውድ ውጭ የሚቀርቡ እና የተነካኩ ምስሎችን ባለማጋራት ለሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መቀነስ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበርክት።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::