በአቶ ወርቁ አይተነው ስም እና ምስል የተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች!

በአቶ ወርቁ አይተነው ስም እና ምስል የተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች! 

የባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነውን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች እንዲሁም የትዊተር አካውንት መኖሩን ተመልክተናል። በርከት ያሉ ተከታታዮቻችንም ገጾቹ አካውንቶቹ የአቶ ወርቁ ስለመሆናቸው እንድናጣራ ጠይቀውናል። 

ኢትዮጵያ ቼክ የገጾቹንና የአካውንቶቹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አቶ ወርቁን አነጋግሯል። አቶ ወርቁ አንድ የፌስቡክ አካውንት እንዳላቸው የገለጹ ሲሆን ይህም በአሁኑ ወቅት ከ132 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ነው። ትዊተርን በተመለከተ ምንም አይነት አካውንት እንደሌላቸው ጨምረው አስታውቀዋል። 

በአሁኑ ወቅት ከ55 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉትን የፌስቡክ ገጽ ጨምሮ ሌሎች በእርሳቸው ስም የተከፈቱ ገጾች ሀሠተኛ ናቸው ብለዋል። 

የአቶ ወርቁን ትክክለኛ የፌስቡክ አካውንት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይችላሉ:- https://www.facebook.com/WAOilfabrica

K 

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::