ባለፈው ሰኞ የተከሰከሰውን የቻይና ኢስተርን አየር መንገድን አስታኮ እየተሰራጨ ያለ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አርማን የሚያሳይ አሳሳች ቪድዮ!

ሰኞ እለት 130 ሰዎችን ጭኖ ሲበር የተከሰከሰውን የቻይና ኢስተርን አየር መንገድን አስታኮ አንድ የ10 ሰከንድ ርዝመት ያለው ቪድዮ በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። ይህ ቪድዮ የአውሮፕላኑን የመጨረሻ ሰአታት ያሳያል የተባለ ሲሆን በቻይና እና ህንድ ማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች በስፋት ተጋርቷል።

ቪድዮው ከአውሮፕላን መስኮት አካባቢ የተቀረፀ እንደሆነ የሚያመላክት ሲሆን አውሮፕላኑ ዝቅ እያለ ሲሄድ የሚጮሁ መንገደኞችን ድምፅ ያሰማል። የአውሮፕላኑ ክንፍ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መለያ አርማ ይታያል።

ኢትዮጵያ ቼክ ቪድዮው ላይ ባደረገው ማጣራት ከምስለ-በራራ ቪድዮ (simulation video) ላይ የተወሰደ እንደሆነ አረጋግጧል።

ቪድዮው X-Plane 11 በተባለ ሶፍትዌር አማካኝነት የዛሬ ሶስት አመት ቢሾፍቱ አካባቢ የተከሰከሰውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለማስመሰል ተደርጎ በሶፍትዌሩ አማካኝነት የተቀናበረ ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::