በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ስም እና ምስል ተመሳስሎ የተከፈተ የትዊተር አካውንት! 

የዛሬ ሶስት ወር ገደማ በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ስም እና ምስል ተመሳስሎ የተከፈተ የትዊተር አካውንት እንዳለ ተመልክተናል። አካውንቱ የአቶ አህመድ እንዳልሆነ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል። 

አካውንቱ አሁን ላይ 950 ገደማ ተከታዮች ያሉት ሲሆን በርካታ መረጃዎችን ከገንዘብ ሚኒስቴር ትክክለኛ የትዊተር አካውንት ላይ እያጋራ (ሪትዊት እያረገ) ይገኛል፣ ይህም ሀሰተኛ አካውንቶች ተአማኒነትን ለማግኘት አዘውትረው የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው። 

አሁን አሁን ከሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ባልተናነሰ ተመሳስለው የሚከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች ከፍተኛ ችግር እየሆኑ ይገኛሉ። ሰሞኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አርማን በመጠቀም እና ‘Ministry of the Finance- Ethiopia’ በሚል ስም የተከፈተ የፌስቡክ ገፅ እንዳለ ኢትዮጵያ ቼክ ለተከታታዮቹ አቅርቦ ነበር። 

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች እንጠብቅ የሁልግዜ መልዕክታችን ነው።

ትክክለኛ እና ማረጋገጫ (verification) ያላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር አካውንቶች:

ትዊተር: https://twitter.com/MoF_Ethiopia?t=vNR5ALM4yL3NoHrBp1FQ9g&s=09

ፌስቡክ: https://www.facebook.com/MoFEthiopia

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::