በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ስምና ምስል የተከፈተ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት!

በርካታ የመንግስት ባለስልጣናትና መንግስታዊ ተቋማት የሚከተሉት በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ስምና ምስል የተከፈተ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት!

አሁን ላይ ከ12,200 በላይ ተከታዮች ያሉትና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈተ የትዊተር አካውንት መኖሩን ተመልክተናል።

አካውንቱ እ.አ.አ በነሃሴ ወር 2021 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን ለሚለጥፋቸው መልዕክቶች በሺዎች የሚቆጠር ምላሽ ከተከታዮቹ እንደሚያገኝ አስተውለናል። ከአካውንቱ ተከታዮች መካከል የመንግስት ባለስልጣናትና መንግስታዊ ተቋማት ይገኙበታል።

ኢትዮጵያ ቼክ የአካውንቱን ትክክለኛነት ለማወቅ ወ/ሪት ፍሬህይወትን መረጃ የጠየቀ ሲሆን አካውንቱ የእርሳቸው አለመሆኑን አሳውቀዋል፣ ምንም አይነት የትዊተርም ሆነ የፌስቡክ አካውንት እንደሌላቸውም ጨምረው ገልፀዋል።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::