የፍትህ ሚንስትር በሆኑት በአቶ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ስምና ፎቶን በመጠቀም የተከፈተ የትዊተር አካውንት መኖሩን ተመልክተናል!

አካውንቱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የተከፈተ ሲሆን አሁን ላይ ከ2,240 በላይ ተከታዮች አሉት። የፍትህ ሚኒስቴር ይህ የትዊተር አካውንት የአቶ ጌዲዮን አለመሆኑን ዛሬ አስታውቋል።

አቶ ጌዲዮን ምንም አይነት የትዊተር አካውንት እንደሌላቸው የገለጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከላይ በተጠቀሰው ሀሠተኛ አካውንት የሚተላለፉ መልዕክቶችም የሚኒስትሩ አለመሆናቸውን ጨምሮ አስታውቋል።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::