በአቢሲኒያ ባንክ ስም እና ሎጎ የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል!

በአቢሲኒያ ባንክ ስም እና ሎጎ የተከፈተ አንድ የቴሌግራም ቻናል በርካታ አነጋጋሪ መልእክቶችን እያሰራጨ ይገኛል። አሁን ላይ ከ150,000 በላይ ተከታይ ያለው ይህ ቻናል የብዙዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ያልተረጋገጡ እና ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጋራት ላይ ይገኛል። 

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ የአቢሲኒያ ባንክን የህዝብ ግንኙነት ቢሮ አናግሯል። ከባንኩ የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው ይህ ቻናል የድርጅቱ አይደለም፣ የሚተላለፈው መልእክትም የባንኩ አይደለም። የባንኩ ትክክለኛ ቻናል 1,445 አባላት ያለው ነው (ሊንክ: https://t.me/BoAEth)። በባንኩ ስም ሌሎችም የተከፈቱ አካውንቶች መኖራቸውን ያሳሰበ ሲሆን የባንኩ አለመሆናቸውን ተጠቅሷል። 

ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ይከላከሉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::