የቴሌ ብር ስምና የንግድ ምልክትን በመጠቀም የተከፈቱ የቴሌግራም ቻናሎች እና ቦቶች!

የቴሌ ብር ስምና የንግድ ምልክትን በመጠቀም የተከፈቱ የቴሌግራም ቻናሎች እንዲሁም ቦቶች የተለያዩ ሽልማቶችን የሚያስገኙ ውድድሮች እንዳሉ በማስመሰል መልዕክት እንደሚያሰራጩ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች ጥቆማ አድርሰውናል። 

በነዚህ የቴሌግራም ቻናሎችና ቦቶች ከሚተላለፉ መልዕክቶች መካከል ወደ ቴሌ ብር ቦት ሰዎችን ከጋበዙ “ጥቅል ዳታ እና የበዓል ስጦታ ገንዘብ” እንደሚያገኙ የሚገልጹ ይገኙበታል። 

ኢትዮጵያ ቼክ ጥቆማውን ተመርኩዞ ከኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ጠይቋል። ከኢትዮ ቴሌኮም ባገኘነው መረጃ መሰረት ቴሌ ብር ሽልማት የሚያስገኙትን ጨምሮ ሌሎች መልዕክቶችን የሚያስተላልፈው ከ96,300 በላይ ተከታዮች ባሉት ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናሉ ብቻ ነው። 

ትክክለኛውን የቴሌ ብር  የቴሌግራም ቻናል የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይችላሉ:- https://t.me/telebirr

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::