በአቶ ወርቁ አይተነው ስም እና ምስል ከተከፈተ ሀሰተኛ የቴሌግራም ቻናል እንጠንቀቅ!

ከቅርብ ግዜያት ወዲህ ታዋቂ ሰዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ ድርጅቶችን፣ አርቲስቶችን፣ ፖለቲከኞችን ወዘተ አስመስለው የሚከፈቱ የማህበራዊ ሚድያ አካውንቶች በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩ ይገኛሉ። ከነዚህ መሀል አንዱን ዛሬ እንጠቁማችሁ:

“የገና ስጦታ ከወርቁ አይተነው” በሚል ርዕስ የያጋሩ እና ይሸለሙ መልዕክቶችን በባለሀብቱ ስም እና ምስል የሚያሰራጭ 11,000 ገደማ ተከታይ ያለው የቴሌግራም ቻናል እንዳለ ተመልክተናል።

ቻናሉ “ዘመናዊ አውቶሞቢል ለ100 እድለኞች፣ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ለ150 እድለኞች፣ ዘመናዊ ስማርት ስልኮች ለ3,000 ባለእድሎች፣ በወኪልነት የመስራት ለ1,000 እድለኞች” ባለሀብቱ እንዳዘጋጁ ይጠቅስና ይህንን ለማግኘትም ቻናሉን ለ50 ሰዎች ማጋራት ግዴታ እንደሆነ ያስቀምጣል።

ይህ የቴሌግራም ቻናል ሀሰተኛ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

ከዚህ ቴሌግራም ቻናል በተጨማሪ በግለሰቡ ስም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች እንዲሁም የትዊተር አካውንት መኖሩን ከዚህ በፊት ለተከታታዮቻቸው ጠቁመን ነበር።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራሳችንን ከተዛቡና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች እናርቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::