ዛሬ ያወጣነዉ መግለጫ የለም”— የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ለኢትዮጵያ ቼክ

መስከረም 02፣ 2015

ይህ በምስሉ ላይ የሚታየዉ ሁለት ገጾች ያሉት መረጃየኦሮሞ ነፃነት ግንባር መግለጫበሚል በማህበራዊትስስር ገጾች እየተጋራ ይገኛል። መረጃዉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ስም እና አርማ በመጠቀም የተጻፈ ሲሆንበተለይ ፌስቡክ ላይ በስፋት እየተጋራ መሆኑን ተመልክተናል።

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የኦነግ መግለጫበሚል በእንግሊዘኛ ቋንቋ በዛሬው ቀን የተጋራዉ መረጃ የህዝቦችንስም በመጥቀስ የተጻፈ የጥላቻ ንግግርን በውስጡ ይዟል።

የመረጃውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ቼክ የኦነግ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ለሚ ገመቹን አናግሯል።

እርሳቸዉም ፓርቲያቸዉ ዛሬ መስከረም 02 2015 ያወጣዉ መግለጫ እንደሌለ ነግረዉናል።

በመጀመሪያ ዛሬ ያወጣነዉ መግለጫ የለም። ቀጥሎም እንደዚህ አይነት ያወጣነዉ መግለጫ የለምብለዋል።

መግለጫ ስናወጣ በድረገጻችን እና የተረጋገጠ (verified) ፌስቡክ ገጻችን እናጋራለን። ስለዚህ ሀሰተኛ ዜናነዉሲሉም መረጃዉ ትክክለኛ እንዳልሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግረዋል።

የኦነግን የፌስቡክ ገጽ እና ድረገጽ የተመለከትን ሲሆን መረጃዉ በገጾቹ ላይ የሌለ መሆኑን አረጋግጧል።

ከዚህ ቀደም ታዋቂ ግለሰቦችንና ተቋማትን በመጥቀስ ሀሰተኛ መረጃዎችን ማጋራት የተለመደ ቢሆንም ሀሰተኛመግለጫ ጽፎ ማጋራት ግን የተለመደ አይደለም።

ስለዚህም ታማኝ ካልሆኑ የመረጃ ምንጮች በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚጋሩ መረጃዎችን ከማመናችን እናማጋራታችን በፊት እዉነተኛነታቸዉን እናረጋግጥ።

በተጨማሪም ወደተጠቀሱት ግለሰቦች ወይም ተቋማት በማህበራዊ ትስስር ገጽ ወይም ድረገፅ በመሄድመረጃዉ እዉን በነሱ የተጋራ መሆኑንም እናረጋግጥ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::