የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የዶክተር ሙሉ ነጋን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈተ የፌስቡክ ግሩፕ መኖሩን ተመልክተናል!

‘Mulu Nega Kahsay’ የሚል ስያሜ ያለው ይህ ግሩፕ በየካቲት ወር 2013 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን አሁን ላይ ከ8,100 በላይ አባላት አሉት።

በግሩፑ በአብዛኛው ጥራታቸው ያልተረጋገጠ የተለያዩ መድሃኒቶችና አበረታች ንጥረ ነገሮች እንዲሁም ከማጭበርበር ጋር የተገናኙ መልዕክቶች ሲጋሩበት አስተውለናል።

ዶክተር ሙሉ ግሩፑን በተመለከተ ከሰዎች ጥቆማ እንደደረሳቸውና በስማቸው ከተከፈተው ከዚህ የፌስቡክ ግሩፕ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቀዋል።

ከፌስቡክ የስነ-ምግባር መርሆች ጋር አብረው የማይሄዱ የፌስቡክ ግሩፖችን ሲመለከቱ የሚከተለውን ሂደት በመከተል ሪፖርት ያድርጉ:
1. ሪፖርት ማድረግ ወደ ፈለጉት ግሩፕ ያምሩ
2. ቀጥሎ ከላይ በስተቀኝ የሚገኙትን ሶስት የነጠብጣብ ምልክቶች (…) ይጫኑ
3. ከዛም በግሩፑ ያዩትን እንከን ይምረጡ
4. ቀጥሎ ‘Next’ የሚለውን ይጫኑ
5. በመጨረሻም ‘Done’ የሚለውን ይጫኑ

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::