በዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጽ!

በዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጽ!

በዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስም የተከፈተ እና ከ41 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ባለፉት ሳምንታት ጥያቄ የሚያስነሱ በርከት ያሉ ይዘቶችን ሲያጋራ እንደነበር ታዝበናል።

ይህ ገጽ የማስመሰል ስራ እየሰራ እንደሆነ የሚያመላክቱ የቋንቋ አጠቃቀሞችን እንዲሁም ምስሎችን በመመልከታችን ለማጣራት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የኮርፖሬቱን ኃላፊዎች አነጋግረን ነበር።

በምላሹም ከ41 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እና ህዳር 16 2012 (እ.ኤ.አ. November 26, 2019) የተፈጠረው ይህ የፌስቡክ ገጽ ተመሳስሎ የተፈጠረ ሀሰተኛ ገጽ እንደሆነ ያነጋገርናቸው የስራ ኃላፊ አረጋግጠውልናል።

“ሀሰተኛ አካውንቱን ለማዘጋት ከፌስቡክ ጋር እየተነጋገርን ነው” ብለዋል የስራ ኃላፊው።

አክለውም ሰኔ 20/ 2005 (June 27, 2013) የተፈጠረው እና ከ625 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ የዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት አ.ማ. ትክክለኛው ገጽ መሆኑንም ገልጸዋል።

በፌስቡክ ማረጋገጫ (verification) ያለውን የዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ትክክለኛ የፌስቡክ ገጽ ቀጥሎ ባለው መስፈንጠሪያ በመከተል ያገኙታል።

https://www.facebook.com/waltainfo/

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::