በፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ስም እና ምስል ተከፍቶ የሚገኝ የፌስቡክ ገፅ! 

ከሰሞኑ በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስም እና ምስል የተከፈተ አንድ የፌስቡክ ገፅ በርካታ አነጋጋሪ መልእክቶችን እያሰራጨ ይገኛል። አሁን ላይ ከ30,000 በላይ ተከታይ ያለው ይህ ገፅ የብዙዎችን ትኩረት ሊስቡ የሚችሉ ያልተረጋገጡ እና ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጋራት ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ ከ5,000 በላይ ተከታዮችን አግኝቷል። 

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስን ዛሬ ጠዋት አናግሯል። ፕ/ር በየነ ገፁ የርሳቸው እንዳልሆነ የገለፁ ሲሆን ህዝብም እንዲህ አይነት በሀሰት የተከፈቱ ገፆች ላይ ጥንቃቄ ሊያረግ ይገባል ብለዋል። 

“እኔ እንደዚህ አይነት ገፅ እንዳለም እውቀት የለኝም። እኔ የሶሻል ሚድያ ተጠቃሚ አይደለሁም፣ ይህ የተባለው ገፅ ፌክ መሆኑን ላረጋግጥ እወዳለሁ” ብለዋል። 

ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ይከላከሉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::