በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ስም እና ምስል የተከፈቱ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፆች! 

የአርቲስት ነፃነት ወርቅነህን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ በርካታ የፌስቡክ አካውንቶችና ገጾች መኖራቸውን ተመልክተናል። 

ከገጾቹ መካከል ከ98 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል። ይህ ገጽ የአርቲስቱን ፎቶዎች፣ ወደ ዩትዩብ የሚያመሩ ማስፈንጠሪያዎችንና ሌሎች ይዘቶችን የሚያጋራ ሲሆን በርካታ ግብረመልሶችን እንደሚያገኝ አስተውለናል። 

ከዚህ ገጽ በተጨማሪም ሌሎች በአርቲስቱ ስም የተከፈቱና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሏቸው የፌስቡክ ገጾች የሚገኙ ሲሆን ማስታወቂያዎችንና ሌሎች ይዘቶችን ያጋራሉ። 

ከወራት በፊትም ከ240,000 በላይ ተከታይ ያለው በአርቲስቱ ስም እና ምስል የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ እንደነበር ኢትዮጵያ ቼክ ለተከታታዮቹ አሳውቆ ነበር።

ኢትዮጵያ ቼክ የገጾቹን ትክክለኛነት በተመለከተ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህን የጠየቀ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት የፌስቡክ ገጾች የሱ አለመሆናቸውን አስታውቋል።

የአርቲስቱ ትክክለኛ የፌስቡክ አካውንት የሚከተለውን ማስፈጠሪያ በመከተል ማግኘት ይችላሉ: https://www.facebook.com/netsanet.workneh.7

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል  ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንጝሮች እንጠብቅ የሁልግዜ መልዕክታችን ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::