አዲስ የተሾሙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ስምና ምስልን በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች መኖራቸውን ተመልክተናል!

ኢትዮጵያ ቼክ የገጾቹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የክልሉን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህን የጠየቀ ሲሆን እነዚህ ገፆች ትክክለኛ እንዳልሆኑ እና ዶክተር ይልቃል ከፋለ ምንም አይነት የፌስቡክ አካውንት እንደሌላቸው አስታውቀዋል።

“አሁን ምንም አይነት የፌስቡክ ገጽ የላቸውም፣ ሁሉም ሀሰተኛ ናቸው። በቅርቡ የፌስቡክ ገጽ ለመክፈት አስበናል” ብለዋል።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::