በዶ/ር ሰማ ጥሩነህ ስምና ፎቶ የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ! 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪ የሆኑትን የዶክተር ሰማ ጥሩነህ ስምና ፎቶ በመጠቀም የተከፈተና “ሰማ ጥሩነህ ሽፈራው – Sema Tiruneh Shiferaw” የሚል መጠሪያ ያለው የፌስቡክ ገጽ መኖሩን ተመልክተናል። ገጹ በነሐሴ ወር 2013 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን በአሁኑ ሰዐት ከ4,600 በላይ ተከታዮች አሉት። 

በገጹ ላይ የተለያዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች የሚጋሩ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠር ግብረመልስ እንደሚያገኙም አስተውለናል። የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም የገጹን ትክክለኛነት እንድናጣራላቸው ጠይቀውናል። 

ኢትዮጵያ ቼክ የገጹን ትክክለኛነት በተመለከተ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት በኩል የጠየቀ ሲሆን ከላይ የተጠቀሰው የፌስቡክ ገጽ የእርሳቸው አለመሆኑን ዶክተር ሰማ ጥሩነህ አሳውቀዋል። በተጨማሪም ዶክተር ሰማ ጥሩነህ ምንም አይነት የፌስቡክ ገጽ እንደሌላቸው ገልጸዋል። 

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች እንጠብቅ የዘወትር መልዕክታችን ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::